Sunday, March 18, 2012

ቅማንት


ቅማንት የብሔር ሥም ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ በጎንደርና አካባቢዋ እንዲሁም በእስራኤል እና በመላ ኢትዮጵያ ተሠራጭተው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ እኒህ ኩሻዊ ሕዝቦች በአሁኑ ሠዓት ቋንቋቸው ከ 1960ዎቹ ጀምሮ በመጥፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሕዝቦቹ ቀደምት አይሁዳዊ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ክርስቲያን ሕዝቦች ናቸው፡፡ ባጠቃላይ 172000 የሚሆኑ እንደሆነ ቢነገርም አብዛኛዎቹ የብሔሩ ተወላጆች በሕዝብ ቆጠራ ወቅት በአማራነት እንደሚመዘገቡ ታዉቋል፡፡ ቅማንቶች በድሮ ሃይማኖታቸው ቄስ ወይም የሃይማኖት መሪ ያላቸው ሲሆን ስሙም ወንበር ይባላል፡፡ ወንበሩ ነጭ ሻሽ ይጠመጥማል በእጁ ግን እንደ ክርስቲያን ቀሳዉስት መስቀል አይዝም፡፡ ወንበሩ የጎደፈ ነገር ይፀየፋል፤ አራስ ቤት አይገባም፡፡ ለእምነቱ እጅግ ጠንቃቃ ነው፡፡

ቅምሻ
ክመንትነይ ....................አማረኛ
I
ወፈለኔኒን ----------- ምን ፈልገህ ነው
ወፈለጌያ----------- ምን ትፈልጋለህ
-ወፈለገት ----------- እሷ ምን ትፈልጋለች
ፈጉናፈለገሁ ----------- ማረፍ እፈልጋለሁ
ኪንትና ፈለገት ----------- መማር ትፈልጋለች
ኒንኝል ፈይነ ፈለገሁ ----------- ወደ ቤቱ መሄድ ይፈልጋል
ወፈለጌናግ ----------- ምን ትፈልጋላችሁ
ጎንደር þልነፈለገሁ ----------- ጎንደርን ማየት እፈልጋለሁ
ናማ¦ሊል ፈይነ ፈለገኩን ----------- ወደ ጓደኛቸው መሄድ ይፈልጋሉ
ናይ ወፈለገናግ ----------- እሳቸው ምን ይፈልጋሉ
አኒ ሸወን ንኝል ፈይን ፈለገሁን ----------- ወደ ፀሎት/ልመና/ቤት መሄድ እፈልጋለሁ
II
አውት ፈተሳግኒ -----------የት እየሄድክ ነው
አያ ፈይሳግ ----------- ወደ ገቢያ እየሄድኩ ነው?
አውት ፈተሣግኒ ----------- የት እየሄደች ነው?
ኒሽ ጉሩዋል ፈተሣግˉጋላ ----------- ወደ ባሏ እየሄደች ነው
አውት ፈየሣግኒ ----------- የት እየሄደ ነው?
- ይወኔዋ ፈሣግ ጋላ ----------- ወደ ሚስቱ እየሄደ ነው
አውት ፈየትናግኒ ----------- የት እየሄዳችሁ ነው?
ሽሌ ፈይነሳግ ጋላ ----------- ወደ ጭልጋ እየሄዱ ነው
ናዴው አውት ፈይነስ አግኒ ----------- የት እየሄዱ ነው
ናንግል ፈይነሣ ጋላ ----------- ወደ ቤታቸው እየሄዱ ነው
ናይ አውት ፈይነስ አግኒ ----------- የት እየሄዱ ነው
ናኹርል ፈይነሳ ጋላ ---------- ወደ ልጆቻቸው እየሄዱ ነው